ዓለምነህ በአዋዜ ፐሮግራሙ ላይ ጸጋዬ አራርሳ ‹‹ኢትዮጵያዊ ማንነት የለም›› ያለውን ይዞ በለዘበ ቋንቋና በለዘበ ድምጽ ደቁሶታል፤ ብዙ ሰዎች የገባቸው አልመሰለኝም፤ በጉዳዩ የተማረውና የተመራመረው ዶር. ጸጋዬ አራርሶም የገባው አይመስለኝም፤ እስቲ እኔ የገባኝን ልንገራችሁ፡፡ በመጀመሪያ በሁለቱ ሰዎች መሀከል ያለውን የትምህርት ደረጃ ልዩነት ዓለምነህ ራሱ እንዳለው እሱ ‹‹በትምህርት እጅግም አልገፋም›› ጸጋዬ ግን የትምህርቱን ደረጃ ጣራው ላይ አድርሶታል ተብሎ […]
↧