አዳም በበደለ መድኃኔ ዓለም ካሠ፤ የተጠቀሰውን አባባል የማያውቅ ክርስቲያን ያለ አይመስለኝም፤ ለእስላሞችም ቢሆን አዲስ ነገር አይሆንባቸውም፤ አዳም ትእዛዝ ጥሶ ዕጸ በለስን በላና ተረግሞ ከገነት ወጣ፤ አዳም በደለ የሚባልበት ምክንያት ይህ ነው፤ አዳም በገነት ባካሄደው አብዮት የተነሣ የሰው ልጆች ሁሉ ከገነት እንደወጡ የሚቀሩ ሆነ፤ ስለዚህም እግዚአብሔር አዘነ፤ በዚህም ምክንያት እግዚአብሔር ወልድ ከሰማየ ሰማያት ወረደና ከድንግል ማርያም […]
↧