በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ‘የማንነት’ እና ‘የብሔር’ ፖለቲካ ወይም ጥያቄ ተምታተዋል። ብዙ ግዜ ሁሉም ነገር ‘የብሔር ጥያቄ’ ነው፤ መልሱም የሚገኘው ‘በብሔርተኝነት’ ነው የሚባለው ጉዳይ ከማንነት ጋር የተያያዘውን ጥያቄ ያድበሰብሰዋል። እንዲያውም አንዳንዴ ብሔርተኝነት ችግሩን ሊያባብሰው ይችላል። የማንነት ወይም የብሔር ትርጉሙም እንዲሁ የተምታታ ነው። ምክንያቱም ማንነትም ይሁን ብሔር በተለምዶ የሚበየነው በቋንቋ ላይ ተመሥርቶ ነው። ስለዚህም በተምታታ ትርጉም ላይ […]
↧
በማንነት ማፈናቀልን እንዴት መቀነስ ይቻላል?
↧
የታሪክ ፈተናችን እና ያሬዳዊ ትዝታ፤ ከክላሽ እስከ ብዕር!
የለውጥ ውርጃ፣ የዘመናዊነት መጨናገፍ፣ የህዝባዊ ኃይል (ድምጽ) ተጽኖ ፈጣሪነት መኮላሸት፣…ድግግሞሻዊ የታሪክ አዙሪት አምሳያ የሆነችው ኢትዮጵያ፤ በተከታታይ ትውልዶች የደም ጎርፍ እየተንሳፈፈች እዚህ ደርሳለች። የአገር ግንባታ ሲሚንቶ ውሉ አልይዝ ብሎ ንቃቃት በዝቶበት የታሪክ ፈተናዋን መሻገር የተሳናት ኢትዮጵያ፤ በውስጣዊ ቅራኔ እንደተናጠች፣ ቅራኔዎቹ በተከታታይ ትውልዶች የደም ጎርፍ ከቶም እየተባባሱ የማህበራዊ ትስስሮሽ ነባር ህሊናዎች እየተናጉ፣ ዘውጋዊ መስመሮች በስታሊናዊ “ዕይታ” የልዩነት […]
↧
↧
የሱሪ ረዥሙ “ፕሮፌሰር ጄኔራል” ሳሞራ የኑስ ስንብትና የሳዕረ መኮንን መንገሥ
ግንቦት 30/2010 ዓ.ም አዲስ አበባ፣ ማምሻውን ከወደ ታችኛው ቤተ-መንግሥት የተሰማው ዜና የኢትዮጵያዊያንና የዓለምአቀፉን ሚዲያ ትኩረት የሳበ ነበር። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ (መከላከያ በአዲሱ አወቃቀር በኮሚቴ (ወታደራዊ ካዉንስል) ሊመራ ነው) በሚል ርዕስ ከሦስት ሳምንት በፊት መከላከያ ሠራዊት እንደተቋም በአመራሩ ላይ ብወዛ ሊያደርግ መሆኑን የሚገልጽ መረጃ ወደአንባቢያን አድርሶ ነበር። በወቅቱ ወደ አንባቢያን ባደረስነው መረጃ ላይ፡- መከላከያ ሠራዊት ሪፎርም […]
↧
ሁለቱ ጄኔራሎች
ብ/ጀኔራል አሳምነው ጽጌ እና ሜ/ጀኔራል አለምሸት ደግፌ ከመከላከያ ሰራዊቱ በተለያየ ጊዜ “የመከላከያ ሪፎርም አደናቃፊ” በሚል ማዕረጋቸው ተገፍፎ የተሰናበቱ ወታደራዊ መኮንኖች ናቸው። ብ/ጀኔራል አሳምነው ጽጌ የቀድሞ የጦር ሠራዊት አባል የነበረና በ1978 ዓ.ም ኢህዴንን የተቀላቀለ ጀግና አዋጊ እንደሆነ የኢህዴን ጓዶቹ ሳይቀር ይመሰክሩለታል። ድህረ-ደርግ በሲቪል አስተዳዳሪነት የላስታ ወረዳ አስተዳደር ቀጥሎም የሰሜን ወሎ ዞን አመራር ሆኖ ሰርቷል። የባድመ ጦርነት […]
↧
ህወሓት እነ ዓቢይን ለመገምገም ኢህወዴግን ስብሰባ ጠራች
ላለፉት ሁለት ቀናት መቀሌ መሽጋ ስትንጫጫ የቆየችው ህወሓት እነ ዓቢይ አህመድን ለመገምገም ስብሰባ ይጠራልኝ ብላ መግለጫ አውጥታለች። የዛሬውን አያድርገውና ዱሮ በፈለገችው ጊዜና ሰዓት ስብሰባ ስትጠራ የኖረችው ህወሓት ለዚህ መብቃቷ ክስረቷን ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል። ህወሓት ይህንን ስትጠይቅ የሚከተሉትን መሠረታዊ ውሳኔዎች በመቀበል ነው፤ ኢትዮጵያ ህዝብታት ወያናይ ዴሞክራሲ ግንባር (ኢህወዴግ) ወይም በአማርኛ ኢህአዴግ፤ “የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሙሉ በሙሉ […]
↧
↧
“አባ ነቅንቅ” –ኦባንግ ሜቶ ሊሞሸር ነው!!
ከኢትዮጵያውያን ጋር ሁሉ የማይሰበር የጽናት ጋብቻ እንደመሠረተ ያምናል። ከሞት ወዲያ ሳይሆን ለሞት ወዲህ ስላለው ታላቅ አገራዊ ክብር ይጨነቃል። በሁሉም ስፍራ፣ በየትኛውም አጋጣሚ ለሚፈልጉት ሁሉ “አለሁ” የሚል ኢትዮጵያዊ ነው። ዘረኝነትን፥ ዘውገኝነትን፥ ጎሠኝነትን፥ አጥብቆ ይዋጋል፤ ይጸየፋል። ከዘር ቆጠራና ከቂም የጸዳች ኢትዮጵያን ማየት ህልሙ ነው። የመጨረሻው ግብ!! ፍቅርን የሚሰብክ በመሆኑ አፍቃሪዎቹ ከልብ ይወዱታል። ለእሱ ያላቸው ፍቅርም ሲሞቅ በማንኪያ […]
↧
“ጄኔራል” አደም መሐመድ፤ ከሬዲዮ ኦፕሬተርነት እስከ መረጃና ደኅንነት ዳይሬክተርነት
ወሎ-አምባሰል የተወለደው አደም መሐመድ በ1975 ዓ.ም ኢህዴንን የተቀላቀለ ነባር ታጋይ ነው። በትጥቅ ትግሉ ወቅት በዋናነት የአዲሱ ለገሰ ሬዲዮ ኦፕሬተር ሆኖ ሰርቷል። አንዳንዶች በሰውየው ላይ ሲቀልዱ “የአዲሱ ለገሰ ሻሂ አፍይ” ይሉት ነበር። አደም መሐመድ ለአዲሱ ለገሰ ለአምልኮ የቀረበ ፍቅር ያለው በመሆኑ በሬዲዮ የሚተላለፉ መልዕክቶችን በጽሁፍ ከመገልበጥና መረጃዎችን ከማድረስ ባሻገር ለሰውየው ማሸርገድ ይወድ ነበር የሚሉት የእርሱ ዘመን […]
↧
ከመቀሌው ዱለታ በስተጀርባ ያሉ እውነታዎች
የህወሃት መግለጫ በመስመሮች መካከል ሲነበብ በተቀማ ጩኸት ሊመሰል ይችላል። ከመቀሌው ዱለታ በስተጀርባ የነበሩ እውነታዎችን ለመዳሰስ የፖለቲካ ሊቅ መሆንን አይጠይቅም።ህወሃቶች አብረው ወስነው ያስተላለፉትን ጉዳይ እንደመጋዣ አኝከው ሲያበቁ፤ ከብዙ ገጽ የክስ ቻርጅ ጋር ብቅ ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩን ለማስጠቆር የሄዱበት ርቀት ግልጽ እና መሳጭ ነው። ሰማይ ወጥተው ቁልቁል ቢወርዱም ግን ከቶውንም የህዝብ ቀልብ ሊስቡ አይችሉም። እኛ ከሌለን ሃገር […]
↧
“የጥላቻና የምቀኝነት አስተሳሰብ መገረዝ አለበት፤ አደገኛ በሽታ ነው”
ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ የአስፈጻሚውን አካል የሥራ ክንውን በተመለከተ ያቀረቡት ሪፖርትና ለጥያቄዎች የሰጡት ምላሽ። ሙሉውን ለመመልከት የቪዲዮው ምስል ላይ ይጫኑ።
↧
↧
የጌታቸው አሰፋ ሌጋሲ እና ቀጣይ አቅጣጫዎች!
የህወሓት ነባር ታጋይ የሆነው ጌታቸው አሰፋ የመረጃና ደህንነት ዳይሬክተር ሆኖ የተሾመው 1993 ዓ.ም ላይ ነበር። ክንፈ ገ/መድህንን የተካው ጌታቸው አሰፋ ከቀደመው የመረጃና የደኅንነት ሰው ፍጹም የተለየ ባህሪ እንዳለው የመረጃ ምንጮቻችን ይጠቁማሉ። ከሒልተን ሆቴል ውጭ እምብዛም የማይዝናናው ጥንቁቁ የመረጃ ሰው ሲበዛ ተጠራጣሪና ደመቀዝቃዛ እንደሆነ ይነገርለታል። በኤምባሲዎች ራት ግብዣ ላይ እንኳን ለመገኘት ከኤምባሲ ኤምባሲ፣ ከአምባሳደርም አምባሳደር የሚያማርጠው […]
↧
Teddy Afro broke his silence to show solidarity with another new breed leader – PM Abiy
Teddy and Abiy are the two new breed leaders I’ve been reviewing their leadership qualities. One is from art while another from politics. In every field and sector, Ethiopia in particular and Africa at large desperately need such new breed leaders to turn the tide and experience a sustainable change in the 21st C. The […]
↧
የአዲስ ኢትዮጵያ ብስራት!
ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) የተመሠረተባቸው አዕማዶች ሁለት ናቸው። እነዚህም ከጎሣ ይልቅ ለሰብዓዊነት ቅድሚያ እንስጥ! እና ሁላችንም አብረን ነጻ ካልወጣን ማንም ብቻውን ነጻ ሊሆን አይችልም! የሚሉት ናቸው። እነዚህን ግዙፍ መርሆዎች ተግባራዊ ለማድረግ የሚጠቀምባቸው ስልቶች ደግሞ ዓመጽ፣ ጥላቻ፣ ክፋት፣ ምቀኝነት፣ ዘረኝነት፣ ወገንተኝነት፣ ወዘተ ሳይሆን ሰብዓዊ ዘርን ከልዩነት በጸዳ ጽኑ ፍቅር በማክበር፣ በመውደድና ለሌላው ሰው ከልብ በመነጨ ቅንነት […]
↧
ደስታዬን ማመቅ አልቻልኩም
ያለንበትን ወቅት ማመን አስቸግሮኛል። ከጥቂት ቀናት በፊት የነበረኝ ግንዛቤ፤ ጠቅልሎ ከኔ ጠፋ። ፍጹም ያልጠበቅሁት ክንውን፤ ገሃድ ሆኖ፤ አይደረግም ያልኩት ተፈጽሞ፤ የሀገራችን የፖለቲካ ሀቅ ተገለባብጦ ሳገኘው፤ ሰውነቴን ዳሰስኩ። የፈለግሁት ሆነ! ብል ስህተትነው። ነገርግን፤ እየተደረገ ባለው ሂደት ያለሁበትን ማመን አቅቶኛል። ደስ ብሎኛል። ሂደቱ መቀጠል አለበት እላለሁ። ደስታዬን ግን ለራሴ አፍኜ መያዝ አልፈልግም። ለዚህም እንኳን ለዚች ቀን እላለሁ። […]
↧
↧
በደቡብ የህወሓት ኅልውና እያከተመ ነው
ለኢህአዴግ ሊቀመንበርነትና ለጠቅላይ ሚኒስትርነት የህወሓት እጩ በመሆን የቀረበውና በህወሓት ሙሉ ድምጽ የተሰጠው ሽፈራው ሽጉጤ ከደቡብ ሕዝብ ሊቀመንበርነቱ ለቀቀ። ሽፈራው ሽጉጤ ራሱ እንደተናገረው ከሆነ “ከሥልጣኔ ለቅቄአለሁ” ቢልም አፍቃሪ ህወሓት የሆኑና እርሱ በኢህአዴግ ሊቀመንበርነት እንዲመረጥ የፕሮፓጋንዳ ሥራ ሲሠሩ የነበሩ ሰውየው “ተገፍቶ ነው” የወጣው በማለት አቅጣጫ የማስቀየር ሙከራ ሲያደርጉ ተስተውለዋል። በቅርቡ በሃዋሳ በደረሰው ግጭት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ […]
↧
አሸባሪው ህወሃት
“ዘረኛ ከሆንክ የዓለማችን ርካሽ ሰው አንተ ነህ” ሠኔ 16 ቀን (ዕለተ ትንሣኤ) 2010 ዓ/ም የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድንና የባልደረቦቹን የለውጥ እርምጃ ለማመስገንና ለመደገፍ በሚሊዮን የሚቆጠረው ህዝብ በመስቀል አደባባይ ይዞ ከወጣቸው መልዕክቶች መካከል አንዱ። “…መግደል መሸነፍ ነው። መግደል መዋረድ ነው። በደስታ አንድ ሆኖ ሀገሬን የሚልን ህዝብ በራሱ ዜጋ ሠዎች አቅዶ አስቦ እንዲጨነግፍ መሥራት ትንሽነት ነው። […]
↧
“ባድመ የኛ አይደለም!” በረከት ስምዖን
በባድመ ጉዳይ የሰሞኑ የህወሓትና የደጋፊዎቹ የማደናገሪያ ጉንጭ አልፋ ሙግት ብዙዎችን ያሰገረመ ከመሆኑ አልፎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድን በፓርላማ በሚያስጠይቅ መልኩ የቀረበ ትዕይንት ሆኖ አልፏል። ራሱ ህወሓት በቆሰቆሰው እሣት የኢትዮጵያን ሕዝብ በ“ድንበር ተደፈረ” ማጭበርበሪያ ካስማገደ እና የፈንጂ ማምከኛ ካደረገ በኋላ አልጀርስ ላይ የአሸባሪና ወንበዴው ህወሓት መሪ በነበረው መለስ ዜናዊ አማካኝነት ባድመን ለኤርትራ አስረክቧል። ከዚያም አልፎ በሌላው […]
↧
ጠ/ሚ/ር አብይ ከኪነ ጥበቡ ማህበረሰብ ጋር
ዛሬ ሰኔ 20፣ 2010 ዓ.ም ጠቅላዩ ከአርቱ ማህበረሰብ ጋር በጠ/ሚ/ር ጽ/ቤት አዳራሽ ከጠዋቱ 03፡00-05፡30 ድረስ በኪነ ጥበብ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል። ምንም እንኳ ከባህልና ቱሪዝም ሚ/ር የታደለው የመጥሪያ ደብዳቤ “ሥልጠና” ቢልም፣ ነገሩ ስልጠና ሳይሆን ውይይት ነበር፤ የውይይት ጊዜ ቢያንስም። ዶ/ር አብይ የ”ሰተቴ” እና “እርካብና መንበር” መፃህፍቶች ደራሲ መሆናቸውንም ነግረውናል። የተወሰኑ ኮፒዎችንም በነፃ አድለዋል። እውነቱን ለመናገር […]
↧
↧
የህወሓት ቁልፍ ሰዎች አሜሪካ ሄደው ጠ/ሚ/ር ዓቢይን ለማውረድ ያቀረቡት ጥያቄ ድራማ
ነባርና ታዋቂ የህወሓት ቁልፍ ሰዎች አሜሪካ መታየታቸው በወፍ በረር ሲዘከር መሰንበቱ ይታወሳል። ከሶስት ሳምንት በፊት የህወሓት ሰዎች አሜሪካ ቤት ለመግዛትና ኑሯቸውን ለማደላደል እንደመጡ ተደርጎ ስም እየተጠቀሰ ሲነገርም ቆይቷል። ተቀማጭነታቸው በአሜሪካ የሆነ የጎልጉል የዘወትር ታማኝ ዲፕሎማት መረጃ አቀባይ ግን ጉዳዩ ሌላ እንደሆነ ነው የሚናገሩት። እንደ ዲፕሎማቱ መረጃ የህወሓት ቁልፍ ሰዎች አሜሪካ ድረስ የመጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ […]
↧
ሕዝብ ከስሜትና ከተራ ብሽሽቅ በመራቅ በያለበት የአገሩ ዘበኛ ይሁን!
ቀደም ሲል በሃዋሳ፣ ባለፈው ቅዳሜ በመስቀል አደባባይ በተቀነባበረ ሁኔታ የደረሰውን የቦንብ ፍንዳታ፣ በቤኒሻንጉል በተለያዩ ቦታዎችና በተለይም በአሶሳ የደረሰንና እየደረሰ ያለውን የዘር ማጥራት ጭፍጨፋ፣ ሕዝብ ወደ ምሬት እንዲሄድ ሆን ተብሎ የሚደረግ የኢኮኖሚ አሻጥር፣ በጥሞና ለምትከታተሉ ሁሉ፤ በባህር ዳር ለጠቅከላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ ቀና ተግባርና የለውጥ ሩጫ እውቅና ለመስጠት የተጠራውን ሰልፍ ለማወክ ከወዲሁ ቦንብ ሲያዘዋውሩ መያዛቸውን ለሰማችሁ፣ […]
↧
የኢትዮ –ሱዳን አዋሳኝ ድንበር ጉዳይ እና የህወሓት መጨረሻ
ለረዥም ዓመታት በሱዳን እና ኢትዮጵያ መካከል የዘለቀው ግንኙነት ወጥ የሆነ መልክ ያለው አልነበረም። የኢትዮጵያ የግዛት ወሰን ከመጽናቱ ቀደም ብሎ በነበሩ ጊዜያት የኢትዮጵያ ነገሥታትና የጦር አበጋዞች በኢትዮ – ሱዳን ጠረፍ አካባቢ ከግብጽ ተስፋፊ ኃይልና ከሱዳን የንቅናቄ (መሃዲስት) ኃይል ጋር ተደጋጋሚ ጦርነት ተፈጥሮ ያውቃል። በአፄ ኢያሱ ብርሃነ ሰገደ የንግስና ዘመን የኢትዮጵያ ድንበር “ገዳሪፍ”ን አልፎ ከሚገኘው “ስናር” እስከተባለው […]
↧