Quantcast
Channel: Goolgule
Viewing all 2896 articles
Browse latest View live

የአ.አ ከንቲባ ጽ/ቤት ጠባቂ ፖሊሶች ተታኮሱ

$
0
0
የአዲስ አበባ መስተዳደር ማዘጋጃ ቤት (ከንቲባ ጽ/ቤት) ውስጥ የሚሰሩ ፖሊሶች ዛሬ በግምት ከቀኑ 6 ሰዓት አካባቢ እርስ በእርሳቸው መታኮሳቸውን አስተዳደሩ ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ፖሊሶቹ የተታኮሱት በከንቲባው ጽ/ቤት ውስጥ የሚሰሩ ፖሊሶች በነበራቸው ግምገማ በተፈጠረ አለመግባባት እንደሆነ ታውቋል፡፡ ፖሊሶቹ የተታኮሱት ከስብሰባው እንደወጡ እንደሆነም ምንጮቹ ገልጸዋል፡፡ በከንቲባ ጽ/ቤት ፖሊሶች በተታኮሱበት ወቅት የአትክልት ተራን ጨምሮ በአካባቢው [...]

ምጽዓት

$
0
0
“በግዞትም ቤት አደባባይ ታስሮ ሳለ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ ኤርምያስ መጣ፡– ሂድ ለኢትዮጵያዊውም ለአቤሜሌክ እንዲህ በለው፤ — የእሥራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤- እነሆ ለበጎነት ሳይሆን ለክፋት ቃሌን በዚህች ከተማ ላይ አመጣለሁ፤ በዚያም ቀን በፊትህ ይፈጸማል፤ በዚያ ቀን አድንሃለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር፤ በምትፈራቸው ሰዎች እጅ አልሰጥህም፤ ፈጽሜ አድንሃለሁ፤ ነፍስህም እንደምርኮ ትሆንልሃለች እንጂ በሰይፍ [...]

በክብር ሲጠበቁ የነበሩት በረከት ለዳግም ህክምና ሳውዲ አረቢያ ሾልከው ገቡ

$
0
0
በልብ በሽታ የሚሰቃዩት አቶ በረከት ስሞኑን ህመሙ ጠንቶባቸው ከሁለት ወር በፊት በሼክ አላሙዲን የግል አውሮፕልና ተጭነው በድብቅ ለህክምና ሳውዲ አረቢያ መግባታቸው ይታወሳል። በወቅቱ ሳውዲ አረቢያ ጅዳ የሚገኝ አንድ «ቡግሻን» እየተባለ የሚጠራ ሪፈራል ሆስፒታል የልብ ቧንቧ ማስፋት  ህክምና ቢደረግላቸውም የባለስልጣኑ የጤነነት ሁኔታ የሚጠበቀውን ያህል ለወጥ ባለማሳየቱ ለዳግም ህክምና ቀጠሮ ተሰጥቷቸው ከሳምታት ቆይታ በኋላ ወደ ሀገር ቤት [...]

የምዕራባዊያን የሕክምና ማዕከላት የሴት ልጅ ግርዛትን ተቀበሉ በስፋትም እየፈጸሙ ነው!

$
0
0
ምዕራባዊያኑ በኛ ላይ ያላቸው ዓላማ ምንድን ነው? በእርግጥም ጽሑፉን ካነበባቹህ በኋላ እንደኔ ሁሉ እናንተም “ምዕራባዊያኑ በእኛ ላይ ያላቸው ዓላማ ምንድን ነው?” እንደምትሉ አልጠራጠርም፡፡ ይሄንን እንድል ያስገደደኝ ጉዳይ አንድ ህክምና ላይ አተኩሮ ጽሑፎችን የሚያትም መካነድር ላይ አንድ ይዝ (ሊንክ) ተጠቁሞ አገኘሁና ከፈትኩት ከዚያ እላቹህ ፈጽሞ ያላሰብኩትና ያልጠበኩት እጅግ ደግሞ የገረመኝን ነገር አገኘሁ፡፡ ምዕራባዊያኑን ስናውቃቸው ብዙ ነገሮችን [...]

“እግዚአብሔር ያሳየዎ: ክርስቶስ ያመልክተዎ!”

$
0
0
እግዚአብሔር በሚያሳየው ክርስቶስ በሚያመለክተው መስመር የማይሰለፍ፤ በቡድንና በጥቅም በተራቆተ ስሜት ተሳስሮና ተለባብሶ የሚኖር ህብረተሰብ፤ ከራሱ በሚፈልቅ ስሜት ወይም ከውጭ በሚመጣ ግፊት ከመጠፋፋት ቢያመልጥም፣ ከመለያየት ማምለጥ ፈጽሞ አይችልም። ክርስቶስም “እርስ በርስዋ የምትለያይ አገር ሁሉ ትጠፋለች። እርስ በርሱ የሚለያይ ከተማ ወይም ቤት አይቆምም” (ማቴ 12።5)በማለት አስጠንቅቋል። ፍረዱብን እያሉ ተቆራኝተው ሰሞኑን ወደኛ በቀረቡት በማህበረ ቅዱሳንና በአባማትያስ መካከል የተከሰተው [...]

በአንድነት ተሰባስበን መታገሉ ግዴታችን ነው

$
0
0
ውድ ኢትዮጵያዊ ድረገጽ፤ ከታች ያለውን ደብዳቤ ለግለሰቦች መላክ ፈለግሁና፤ ለማን ልላክ ብዬ ካወጣሁ ካወረድኩ በኋላ፤ የተወሰኑ ስሞችን ሰበሰብኩ። እኒህን ለይቶ ማውጣቱና፤ እኒህ ብቻ ናቸው ብሎ መለየቱ አሳሰበኝ። ማን ማንን ይወክላል? ሌላውስ ላለመወከሉ ምን መከላከያ አለኝ? እኒህን ለመሰሉ ጥያቄዎች፤ አመርቂ አልስ መሥጠት አልቻልኩም። ለምን በጠቅላላው በትግሉ ላይ ለተሰማሩ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ፤ ይኼ ኃላፊነት አለብን በማለት አልልክላቸውም? የሚለው [...]

መንግስት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ገጥሞታል

$
0
0
የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ የሆነ የውጭ ምንዛሬ እጥረት እንደገጠመው የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡ አንድ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ የብሄራዊ ባንክ ከፍተኛ የኢኮኖሚ አጥኚ እጥረቱ መኖሩን አረጋግጠዋል፡፡ ከ20 ቀናት በፊት እያንዳንዱ የንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የውጭ ምንዛሬ ይሸጥ እንደነበር የተናገሩት ምንጮች፣ ከ20 ቀን ወዲህ ግን በሁሉም የንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ማንኛውም አይነት የውጭ ምንዛሬ እንዳይሸጥ በደብዳቤ (circular ዞሯል) ተከልክሏል፡፡ በመሆኑም [...]

ጎተራው ወዴት ነው?¡

$
0
0
ሀገር በብረት ሲታጠር — ‘ግንቦት ሃያህ’ ሲከበር፤ አዲስ ዓመት በመጣ ቁጥር — ዘመን በዘመን ሲቀየር፤ የስራ-ፈቶች ስብስብ መንጋ — ‘ፓርላማህ‘ሲከፈት ሲዘጋ..፤ ሱፍህን ገጥግጠህ — ከረባትህን ጠፍረህ፣ ወዝህን አሳምረህ — ካሜራ ፊት ቀርበህ፣ ጉሮሮህን..ጠርገህ — ፊትህ የከመርከውን ‘ሃያ ገጽ’ ገልብጠህ፣ ቁጥር እየቆጠርክ፣ አሃዝ እየጠራህ…፣ “ምናምን..ሺ.ቶን፣ ሚሊዮን ስልቻ፣ አምርተን አስገባን በዚህ ዓመት ብቻ…”፣ እያልክ ስትደሰኩር — ትንፋሽህ [...]

“ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ”የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ፕሮግራሙን ይፋ አደረገ

$
0
0
ጥቅምት 12 ቀን 2007 ዓ.ም 9 ተቃዋሚ ፓርቲዎች የመሰረቱት ትብብር “ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ” በሚል ለአንድ ወር የሚቆይ የመጀመሪያ ዙር የህዝባዊ ትግል ፕሮግራሙን ዛሬ ጥቅምት 25/2007 ዓ.ም በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት ይፋ አደረገ፡፡ “ነጻነት በሌለበት ፍትሃዊ ምርጫ የማይታሰብ በመሆኑ የተዘጋውን በር ለመክፈት የ‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ› በሚል የፕሮግራም መርሃ ግብር ለመክፈት ወስኖ የመጀመሪያው ዙር እንቅስቃሴ በአዲስ አበባ ከተማ [...]

የሰላም ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ ፋንታሁን ብርሃኑ ታሰረ

$
0
0
ተቃዋሚ ፓርቲዎችን በማስተባበርና በማቀራረብ እርቅ ለማስፈን እንደሚንቀሳቀስ የሚነገርለት የመግባባት፣ አንድነትና ሰላም (ሰላም) ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ ፋንታሁን ብርሃኑ መታሰሩን ምንጮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ አቶ ፋንታሁን የታሰረው ‹‹የሰላም ጥሪ›› በሚል ነጭ ሰንደቅ አላማ በማውረብለብና የማህበሩን አላማ የሚገልጹ፣ እንዲሁም ማህበሩ በአሁኑ ወቅት ለአገሪቱ ችግር የሚላቸውን ጉዳዮች በዝርዝር የያዘ በራሪ ወረቀት ለህዝብ በመበተን ማህበሩን በማስተዋወቅ ላይ በነበረበት ጊዜ [...]

“እኛ”!! እናንተ እነማን ናችሁ? ደረጃ ምደባ!!

$
0
0
ደረጃ ምደባ ለሸቀጥ ወይም ለአንድ ምርት የሚወጣ ማነጻጸሪያ፣ መለያ፣ መተመኛ፣ የጥራት መጠን መለኪያ … ነው። የደረጃ ምደባ ሲከናወን እንደ አቅሚቲም ቢሆን አስፈላጊ የሚባሉ የመመርመሪያ መሳሪያዎች፣ ቤተ መመርመሪያ፣ መርማሪ ባለሙያና ተመርማሪው ሸቀጥ አስፈላጊ ናቸው። የወጉ አሰራር ካለ ማለት ነው። “እኛ” ሲባል ባጭሩ ከአንድ በላይ ማለት ነው። በሌላ አነጋገር አንድ ብቻውን “እኛ” ሊባልም ሆነ እኛ ብሎ ራሱን [...]

እርም (ሐራም)

$
0
0
በባህላችን የሰው ስም በትርጉም አልባነት እንደማይለጠፍ፤ ከሰውነታችን ጋራ የሚገናኙ ነገሮችም ስማቸው ከመነሻቸው ጋራ የተያያዘ ነው። “እንጀራ” ከምድራዊ ህይወታችን ጋራ ከተገናኙት መሠረታውያን ነገሮች አንዱ ነው። እንጀራ እስካሁን ድረስ የተነሳበትን የታሪክ ትዝታ ተሸክሞ ብዙ ዘመን ተጉዟል። እንጀራ ከወላጅ እናቱ ከጤፍ ጋራ በመተባበር ከኢትዮጵያና ከህዝቧ ጋራ ያላቸው ግንኙነት ሩቅና ጥልቅ ትስስር እንዳለው ሁሉ፤ ከመብላት ስሜትና ሱስ ጋራ ተዋህዶ [...]

THE BRUSSELS ETHIOPIAN HISTORICAL MARCH!

$
0
0
The Woyyane (The TPLF) is a terrorist organisation that is holding Ethiopia at ransom. Since the these criminals came to power, nothing changed in their wild behaviour. They were terrorists yesterday, they are terrorists today and unless they are stopped now, they wouldn’t change their behaviour in the future. The worsening brutality of the ethno-apartheid [...]

“ኢቦላ” – ለድሆች የቀረበ የወረርሽኝ ኢንቨስትመንት!?

$
0
0
በተለያዩ ወቅቶች የሰውን ልጅ ከእንስሳ በማሳነስ የተፈጸሙ ወንጀሎች ስለመኖራቸው መረጃዎች ይወጣሉ። በቤተ ሙከራ ውስጥ የሚፈበረኩትና ሆን ተብለው እንዲሰራጩ የሚደረጉት የበሽታ መነሻዎች የክቡር ሰው ልጆችን ህይወት በሚዘገንን ሁኔታ አራግፈውታል። አባት፣ እናት፣ ልጅ፣ የልጅ ልጅ፣ አልፎ ተርፎ ትውልድ … የሰው ልጅ በሽታ ኢንቨስት ተደርጎበት፣ የሕዝብ ብዛት መቀነሻና የባዮሎጂካል ጦር መሣሪያ መመራመሪያ ተደርጓል፣ አሁንም እየተደረገ ነው፤ የበሽታ ማምከኛ [...]

የልጆቻችን ሀገር

$
0
0
አያቶቻችን የልጆቻችን መሬት ነች ብለው ደማቸውን አፍስሰው ሀገራችንን ከወራሪ ፋሽት ታደጉልን አባቶቻችን በውርስ እርስ በእርስ ሲጣሉ ሳይኖሩበት ሳያኖሩበት ይኸው አሉ ። ልጆች የሚሆነው ሳይገባቸው ውሉ የጠፋባቸውን አባቶቻቸው እያዩ ነው፤ ግራ መጋባታቸውን እየወረሱ ግራ እየተጋቡ ነው ፤ ወይ  በሽሽት ላይ ናቸው፤ ነገር ግን እትብታቸው የተቀበረባትን ቀዬ ከማዶ ሆነው እያዪ የጨው አምድ ሆነው ቆመዋል፤ ብቻ ልቦቻቸው ያነባሉ። [...]

ብርቱካን በሊባኖስ ተረፈች፣ አልማዝ በኦማን የአካል ጉዳተኛ ሆና ቀረች !

$
0
0
የተረፈችው የእህት ብርቱካን ጉዳይ … በሃገረ ሊባኖሰ ቤሩት ከ4ኛ ፎቅ ወድቃ የተረፈችው እህት ብርቱካን ጤንነት የተስተካከለና ከድካም ህመሟ ሙሉ በሙሉ እያገገመች መሆኑን መረጃዎች ማምሻውን ደርሰውኛል። የቆንስል ሃላፊዎች አልማዝን ሲያነጋግሯት በሊባኖስ ቆይታ ስራ መስራት እንጅ ወደ ሀገር ቤት መመለስ እንደማትፈልግ እንደገለጸችላቸው አምባሳደር ሐሊማ ሙሃመድ አጫውተውኛል። በቀጣይ ቀናትም ህክምና እየወሰደች ያለችበትን መካስድ ሆስፒታልን ለቃ እንደምትወጣ ፣ በቤሩት [...]

ዓለም በቃኝ አለ!

$
0
0
ግጥሙን በPDF ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ::

“ለነሱማ…”

$
0
0
ለሕዝቦች አርነት — ላገርህ አንድነት፣ አርቀህ ማለምህ — አሕዛብን ማንቃትህ፣ “..ጠጣሩ እንዲላላ..” ምክር መለገስህ፣ “በረከት” አድርገህ “ርግማን” ማውረድህ..፣ አቤት! “ለነሱማ” እጅግ ማስፈራትህ! እነ-ኮሎኒያሊስት — ደግሞ እነ-እምፔሪያሊስት…፣ ያገርህ ደመኞች፟- ህሊና የለሾች፣ የሞራል፣ የባህል፣ የታሪክ አልቦዎች፣ አጠገብህ መቆም ከቶ ሲሳናቸው፣ እሚያረጉት ሲያጡ — ወኔ ሲከዳቸው፣ ሃቅን ስለሚሸሹ፟- መበለጥን ስለማይሹ፣ ምኑ ነው እሚደንቅህ? “ዕብድ” ነውስ ቢሉህ! ለኛ እንጂ [...]

የማህበረሰብ ውይይት በኢትዮጵያ ዘለቄታዊ ሰላምና ትብብር

$
0
0
በሰሜን አሜሪካና አውሮፓ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ከቅርብና ከሩቅ ተጠራርተው ቅዳሜለት (ኅዳር 6/Nov. 15) በአርሊንግተን ቨርጂኒያ ስብሰባ አድርገው ነበር። ውይይታቸው በኢትዮጵያ ዘለቄታ ያለው ትብብር ለመገንባት የሚያስችሉ አዳዲስ ሃሳቦችና የጋር እሴቶችን በመመርመር ላይ ያተኮረ ነበር። በሰሜን አሜሪካ የሚገኘው የጋራ እንቅስቃሴ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የተባለ የሲቪክ ድርጅት ያሰናዳው ጉባዔ ከተለያዩ ብሄሮች፤ ጾታና የሃይማኖት አባላት፤ እራሳቸውን እንደግለሰብ ወክለው የተሳተፉበት ነበር። ቅዳሜለት [...]

“የደም ከፈን!”

$
0
0
የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር ኦባንግ ሜቶ ለታዋቂው የስዊድን ጨርቃጨርቅ ዓለምአቀፍ ቸርቻሪ H&M Hennes & Mauritz AB (H&M) ፕሬዚዳንትና ዋና ሥራአስኪያጅ ካርል ዮሐን ፔርሶን ከህወሃት/ኢህአዴግ ጋር ስለሚያደርገው የንግድ ውል ኩባንያቸው ሊገጥመው ስለሚችል አደጋ ማስጠንቀቂያ ልከዋል፡፡ ሰኞ በዋሽንግተን ዲሲ በተደረገ ሥነስርዓት ሚ/ር ፔርሶን የ2014 በንግድ የማያዳላ ተሸላሚ መሆናቸውን አስመልክተው በላኩት ደብዳቤ ላይ ኩባንያቸው በኢትዮጵያ ሊጀምር [...]
Viewing all 2896 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>