Quantcast
Channel: Goolgule
Browsing all 2895 articles
Browse latest View live

የጥቁር ሕዝብ ኩራት!

መጪውን የአድዋ ቀን ስናስብ “እምዬ ምኒልክ ምን ዓይነት ውርስ ትተውልን ሄዱ?” ብለን እንድንጠይቅ የሚያደርገን ነው፡፡ በመሆኑም ወደ ጦርነት ለመግባት ሳይፈልጉ “በግድ” ወደሄዱበት የጣሊያን ጦርነት መለስ ብለን የሆነውን እንድናስብ ወደድን፡፡ ክተት፡- “እግዚአብሔር በቸርነቱ እስካሁን ጠላትን አጥፍቶ አገር አስፍቶ...

View Article


ኢትዮጵያ ሀገራችን የሰብአዊ መብት ተሟጋች ልጇን አጣች

በሰብአዊ መብት ተሟጋችነታቸው፣ ለሰላምና ለዲሞክራሲ መስፈን ታጋይነታቸው የሚታወቁት ዶ/ር ማይገነት ሽፈራው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። ዶ/ር ማይገነት ሽፈራው ስለ ሰላም የሰበኩ ያስተማሩና የጻፉ ቀንዲል ኢትዮጵያዊ ነበሩ። ድህነትና በሽታ፣ ርሐብና ስደት፣ አምባገነንትና ጦርነት እያለ የኢትዮጵያ ሴቶች መብት መከበር፣...

View Article


በአዲስ አበባና አካባቢ የታክሲ ሥራ ማቆም ዓድማ እየተካሄደ ነው!

የካቲት 14 የጸደቀውን በተለይ ታክሲዎችን የሚመለከተው የአሽከርካሪዎች ሕግ በመቃወም ለሁለት ቀናት የተጠራው ዓድማ በአሁኑ ጊዜ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በአዲስ አበባ በሁሉም ክፍለከተሞች አድማው እየተካሄደ ከመሆኑ ባሻገር ዓድማውን በመጣስ ታክሲቸውን ሲያሽከረክሩ የነበሩ “አድርባይ ሹፌሮች” ላይ በተለይ በአውቶቡስ ተራ፣...

View Article

ብሶት የወለደው የኦሮሚያ አመጽ ተቆንጥሮ አስመራ ላይ ተላከከ!

በኦሮሚያ የተነሳውን ህዝባዊ እምቢተኛነትና ዓመጽ ተከትሎ ስለጠፋው የሰው ህይወት እርግጠኛ አሃዝ የሚጠቅስ አልተገኘም። ዓለምአቀፍ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶችና የአገር ውስጥ ቀናቃኝ የፖለቲካ ድርጅቶች እንደሚሉት የህወሃት አንጋቾች ከ200 በላይ ንጹሃንን ገድለዋል። በነጻ አውጪ ስም አገሪቱን እየመራ ያለው የትግራይ ሕዝብ...

View Article

“ሀገራችን ላይ እየኖርን አይመስለኝም” ታክሲ አሽከርካሪ

“ሁላችንም የቤተሰብ አስተዳዳሪዎች ነን።ሕጉ ተግባራዊ የሚደረግ ከሆን በአጭር ጊዜ ውስጥ ክሥራ ውጪ እንሆናለን።’’ በዛሬው ዕለት የታክሲ ማቆም አድማ ካደረጉት የታክሲ አሽከርካሪዎች በከፊል፡፡ በአዲስ አበባ የመንገድ ትራፊክ ደኅንነት ደንብን ለማስከበር ከአምስት ዓመት በፊት የወጣውና በከፊል ሲተገበር የነበረው ሕግ...

View Article


ጊዜ በማያደበዘዝው የአድዋ ድል ማግስት…

የዓለም ህዝብ ሁሉ ለመጀመሪያ ጊዜ ነጭን ድል ያደረገውን የጥቁር ጦር መሪ አጤ ምኒልክን ለማወቅ እጅግ ጓጓ፡፡ ምስላቸውን ለማየት ተቁነጠነጠ፡፡ ሙሉ ታሪካቸውን ለመስማት ተንሰፈሰፈ፡፡ ይህንኑ ተከትሎም፤ “እንኳንም ደስ አለዎት” ለማለት ከቁጥር የበዙ ደብዳቤዎች ይጎርፉላቸው ነበር፡፡ ከነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹ በፖስታ...

View Article

አድዋ! 120 ዓመት!

“… የተተከለው ድንኳን ሲታይ ከብዛቱ የተነሳ አፍሪካ ኤሮጳን ለመጠራረግ የተነሳች ይመስላል፡፡ የጦርነቱ ዕለት ኢትዮጵያውያኑ ደማቅ ቀለም ያለው ካባ ለብሰው፤ ጠመንጃና ጦር ይዘው፤ ጎራዴ ታጥቀው፤ የነብር ያንበሳ ቆዳ ለብሰው፤ አዝማሪዎቹ እየዘፈኑ፤ ቄሶች፤ ልጆች፤ ሴቶች ሳይቀሩ ፀሐይዋ ፈንጠቅ ስትል በተራራው ላይ...

View Article

በሪሞት ኮንትሮል ትግል መምራት አለመቻልና ሕብረት በዲያስፖራ

የአዲስ ድምጽ ሬዲዎ ጃንዋሪ 17.2016 3 ሰዎችን፤- 1ኛ. ዶ/ር አረጋዊ በረሄን የትግራዮች ለደሞክራሲያዊ ትብብር ሊቀ መንበር፤ 2ኛ. ዶ/ር በያን አሶቦን ከኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር 3ኛ/ አቶ ተክሌ የሻውን ከሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት አቅርቦ በኢትዮጵያ ጊዜያዊ ሁኔታ ላይ አወያይቷቸው ነበር። በቅድሚያ አቶ...

View Article


ፍቅር እና የትብብር መንፈስ የታየበት ጉባኤ

በኢትዮጵያ ያለውን የፖለቲካና ማህበራዊ ቀውስ አስመልክቶ እሁድ ፌብሩዋሪ 14 ቀን፣ 2016 ከቀኑ 2:00pm 7:30 pm በሳን ሆዜ ከተማ ማሶኒክ ሴንተር፤ የተጠራው ሕዝባዊ ስብሰባ አራት ተናጋሪ እንግዳወች፣ የእምነት አባቶች፣ እንዲሁም ከተለያዩ የሰሜን ካሊፎርኒያ ከተሞች የመጡ በርካታ ኢትዮጵያውያን የተሳተፉበት...

View Article


ከድጡ ወደ ማጡ፣ አሰብ በአረቦች እጅ ገባች

የአገራችን አንድነትና ብሎም ሕልውና በቋፍ ባለችበት በዚህ ቀውጢ ወቅት ውይይቱ ሁሉ ማተኮር ያለበት ለሥጋቶቹ ምንጭና ምክንያት ስለሆኑት ስለ ዴሞክራሲ ደብዛ መጥፋት፣ ስለፍትህ መቅጨጭ. በብሔረሰቦች መካከል ስለሚታዩት ጥላቻና ግጭቶች እነዚህን የወለደው ሥርዓት ስለመለወጥ ብቻ መሆን አለበት ሌላው ሁሉ ገብስ ነው የሚሉ...

View Article

የጃዋር መሃመድ ቅኝቶች

መገናኛ ብዙሃንን መቼ እና እንዴት መጠቀም እንዳለበት ጠንቅቆ ያውቃል። የሚፈልገውን  ነገር ሁሉ ከፈጸመ በኋላ ግን እንደ በረሃ ተኩላ እያደፈጠ ይናከሳል። ሲናከስ ደግሞ ማንንም አይምርም።  ውለታ የሚባል ነገር አያውቅም። ይሉኝታ አይነካካውም። እፍረትም በእርሱ ዘንድ የለችም። ከቶውን መቀበል እንጂ መስጠትን አያውቅም።...

View Article

ህወሃት ራሱን “ሳያጸዳ” በሌላው ዘምቷል

“የኢህአዴግን መርህ እስከተከተለ ድረስ መሃይምም ቢሆን ሚኒስትር እናደርጋለን” ያሉት መለስ ዙሪያቸውን “የበታች” በሆኑ ሹሞች አስከብበው የቆዩት ያለምክንያት አልነበረም፡፡ “አዋቂ፣ ጠቢብ፣ ባለራዕይ፣ ምንተስኖት፣ …” የሚሉ “ማዕረጎችን” አስገኝተውላቸዋል፡፡ ከዚህ አንጻር የፈለጉትን ሥልጣን ላይ ያስቀምጣሉ፤ ከዚያ...

View Article

“የመሬት ባላባቱን” አባይ ማን ይድፈራቸው?

ከተለያዩ አቅጣጫዎች በተቃውሞና ዓመጽ የተወጠረው ህወሃት/ኢህአዴግ በአስሩም ክፍለከተሞች የሚገኙ እስከ 600 የሚደርሱ የመሬት ባለሙያዎችን ካገደ በኋላ የአዲስ አበባ የመሬት አስተዳደር ሞሳኞች ያላቸውን 85 አመራሮችና ሠራተኞችን በቁጥጥር ሥር አውሏል፡፡ “የመሬት ከበርቴውን” አባይ ጸሃዬንስ ማን ይደፍራቸው ይሆን...

View Article


የመለስ ዜናዊ ራእይ

መለስ ዜናዊ ለኢትዮጵያ የጠላት ጠላት ደመኛ ጠላት ነው። ከአባቱ፣ ከእናቱና ከአያቶቹ የወረሰው በኢትዮጵያና በሕዝቧ ላይ የፈጸመው ግፍ፤ የሃገር ማፍረስ ድርጊት በታሪክ የማይረሳ ነው። እሱ ብቻ ሳይሆን የህወሓት አመራርንም ይጨምራል። የስም ዝርዝራቸውን በተለያዩት ጽሁፎቼና ከዚህ በላይም ስላካተትኳቸው እንሱን መመልከትና...

View Article

ኦህዴድ ሳያገግም፤ ብአዴን ሊደገም?

ኢትዮጵያን በተገንጣይ ስም የሚመራው የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግምባር – ህወሃት፣ የገጠመው ቀውስ እየተለጠጠበት ነው። ኦህዴድ አደረጃጀቱ ሊጠገን በማይችልበት ሁኔታ ተናግቶበታል። ይኽው ወረርሽኝ ወደ ሌሎች ገባር ድርጅቶች መስፋፋቱ የማይቀር ቢሆንም ብአዴን ውስጥ ቀውስ ስለመነሳቱ መረጃዎች ከቀድሞው በላይ ጎልተው...

View Article


ህወሃት – 9 ስደተኞችን ደብዳቤ ጽፎ ከአሜሪካ ወሰዳቸው

ከተለያዩ አገራት አሜሪካ ገብተው የስደት ማመልከቻ ያስገቡ 9 ኢትዮጵያውያንን ህወሃት ተረከቦ ወደ አገር ቤት እንደወሰዳቸው ታወቀ። አንዱ ራሱን ለማጥፋት ሞከሮ ነበር። ወደ ኢትዮጵያ ቢሄድም የጤናው ሁኔታ አልታወቀም። ድርጊቱን አስመልክቶ አቶ ኦባንግ ሜቶ “ከህወሃት ተግባር በላይ በራሳችን አዝኛለሁ” ሲሉ ወጣቶቹን...

View Article

ኢትዮጵያን የሚወክሉ የተለያዩ ወገኖች፤

የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ መግለጫ መጋቢት 1፤ 2008ዓም፤ ዋሽንግቶን ዲሲ፤ የአፈጻጸም ማጠቃለያ፤ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) የካቲት 6፤ 2008ዓም (February 14, 2016) በአሜሪካ የሜሪላንድ ጠቅላይ ግዛት ሲልቨር ስፕሪንግ ከተማ ባደረገው ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ “የኢትዮጵያ የዕርቅና...

View Article


ይድረስ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ጉልበት ላላችሁ ሁሉ

ልጆች ሆነን ታላላቆቻችን ጉልበት አለን ብለው በደል ሲፈጽሙ “እግዚአብሔር በቀዳዳ ይየው!” እንል ነበር፤ ለመርገምም እየፈራን አንዲያው ድርጊቱ እንዲመዘገብልን ማሳሰባችን ይመስለኛል፤ አሁንም እንደዚያ ለማለት ይቃጣኛል፤ ግን አግዚአብሔር በሰማይ ላይ መኖሩን፣ በእያንዳንዳችን ውስጥ መኖሩን የቤተ ሃይማኖት ሰዎች እንኳን...

View Article

የዕርቅ ሃሳብ ከውስጥም ከውጭም ትኩረት ስቧል

አሁን ኢትዮጵያ ለደረሰችበት አሳሳቢ ደረጃ ዋናውና ብቸኛው መፍትሔ ሰላማዊ ዕርቅ መሆኑ በአገር ውስጥና በውጪ ልዩ ትኩረት እየሳበ መሆኑ ተሰማ። አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ኢህአዴግ በራሱ ችግር በየጊዜው ከሕዝብ ጋር ቅራኔ ውስጥ መግባቱን፣ ይህንን ቅራኔ መፍታት ካልቻል መንገዱ የውድቀት እንደሚሆን አስጠነቀቁ። ሕዝብ...

View Article

ከተማርኩት ቁጥር 1

ያሜሪካ ቆይታዬ በጣም አጭር ነው። ሁለት አመት እንኳን አይሞላም። ላገሩ አሁንም ላገሩ ባዳ ለወንዙ እንግዳ ነኝ። ገና ብዙ ያልገባኝ ነገር አለ። ግን በዚህች አጭር ጊዜም ቢሆን ብዙ ጠቃሚ ነገር ተምሬያለሁ ብል “አይ ገና ምኑ ተይዞ” እንደማትሉኝ ተስፋ አደርጋለሁ። ለምን ቢባል ልማር ላለ ሳር ቅጠሉ እውቀት መሆኑን...

View Article
Browsing all 2895 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>