ከጥቂት ሳምንታት ወዲህ ባልተለመደ ሁኔታ ኢህአዴግ ላይ ታዋቂ የዓለማችን ጋዜጦች የጀመሩት ተከታታይ ትችት፣ ማሳሰቢያና መፍትሔ ጠቋሚ ዘገባዎች መነጋገሪያ አጀንዳ ሆነዋል፡፡ ሚዲያዎቹ በዘገባቸው ኢህአዴግን ከቻይና አምባገነናዊና አክራሪ አገዛዝ ጋር አመሳስለዋል፡፡ ኢህአዴግ እከተለዋለሁ የሚለውን የኢኮኖሚ መርህ ከቻይና የተኮረጀ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ውጤቱም ሆነ መድረሻው ግራ የሚያጋባና የማይታወቅ እንደሆነ ዘግበዋል፡፡ ጋዜጦቹ ኢህአዴግን በሚንከባከቡት መንግሥቶቻቸው እና በራሱ ኢህአዴግ ላይ [...]
↧