የኢሳት ራዲዮና ቴሌቪዥን (ነጋሪተ ወግና ምርዓየ ኩነት) ጋዜጠኞች ከሕዝባዊ ግንባር መሪ አቶ ኢሳይያስ አፈወርቂ ጋር ያደረጉትን ቃለ መጠይቅ ተከታተልነው፡፡ ያው አስቀድሜ እንደገመትኩት በአሮጌው ድሪቶ ላይ አሮጌ ጨርቅ ድረታና እብለት ክህደት እንጅ የነበረውን አሮጌውንና ያላዋጣውን በመተው በአዲስና በተመከረ በተማረ ልብ አዲስ ሐሳብ አዲስ መንገድ ለመቀየስ አልተፈለገም፡፡ የሚጠበቀውና አስፈላጊው ግን ይሄኛው ነበር፡፡ ለነገሩ ከአንባገነን ሥርዓት ባለሥልጣናት ይሄ [...]
↧