መግቢያ፤ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር፤ ከተመሠረተ ጀምሮ የተለያዩ ስሞችን፣ መርኆዎችን፣ ተግባራትን፣ ባጠቃላይም ማንነትን ተከናንቧል። ይህ ማለት፤ በሂደቱ እየተቀያየረ የሄደ ድርጅት ነው። ሲነሳ፤ አሁን የያዘው እምነት፣ ግብና አሠራር አልነበረውም። እግረ መንገዱን ለዕለቱ የሚረዳውን የፖለቲካ አቋም እየውለበለበ ተጓዘ እንጂ፤ ዘላቂ የሆነ የፖለቲካ አቋም አልነበረውም። ይህ የሚነግረን፤ ይህ ድርጅት፤ አጋጣሚዎችን ተጠቃሚነትን፣ ሥልጣንን፣ ቂምና በቀልን፣ የሕልውናው መሠረቶች አድርጎ የተጓዘ [...]
↧