ህወሃት በዘረፈውና በሚዘርፈው ሃብት ተጠቅሞ ለወዳጆቹ የሚያኮራ፣ ትውልድ ለሚላቸው የሚበጅ ተግባራት እያከናወነ እንደሆነ ይነግረናል፤ ይነግሩናል። ውስን ባለሥልጣናትና አበሮቻችው በሃብት ተመንድገዋል። በንዋይ ሰከረው የሚያደርጉት እስኪጠፋቸው ናጥጠዋል። የት ጋር አንደሚያበቃ ባይታወቅም፣ የተደሰቱ፣ የተከፉ፣ የተናቁ፣ የተሰረቁ፣ የሚሰረቁ፣ እየሰረቁ ያሉ፣ የተትረፈረፈላቸው፣ በስማቸው የሚነገድባቸው፣ ባሪያዎችና ባንዳዎች፣ ቀን የሚጠብቁ፣ ጥርሳቸውን የነከሱ፣ … ወዘተ “አብረው” አሉ፡፡ ዘመን፣ ወራትና ቀናት ቅዠትን በመሰሉበት ዓለም፣ [...]
↧