“የአብዮት ያለህ!”፥ አትበሉ ባ’ገሬ፣ በአብዮት መሃል፥ አብዮት አይጠሬ፣ ምስጋና ቢስ ትውልድ፥ ሆነነው ነው እንጂ፣ የግፈኛን ቀብር፥ የምናበጃጅ፣ የሚሞቱልንን፥ የደም ዋጋ ንቀን፣ በአብዮት መሃል፥ ካ’ብዮት ርቀን፣ በአርበኞች መሃል፥ ባ’ርበኝነት ስቀን… “ደሃ ህዝብ አስፈጁ”፥ ስንል ተሰምተናል፣ “አመሉ ሲታወቅ”፥ ብለን አድንቀናል፣ ‘ያስፈጀው’ ሲወገዝ፥ ፈጂውን ትተናል፣ አህያ እየፈራን፥ ዳውላ መ’ተናል። ልንገርህ ወገኔ፥ አብዮት ሁለት ነው፥ መንታ ነው ፍጥረቱ፣ እርግጥም [...]
↧