ንብረትነቱ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር እንደሆነ በሚነገርለት ካፍቴሪያ ውስጥ የሚፈጸመው ግፍ አይሏል ። ከዛሬ 10 ዓመት በፊት እዚህ ኮሚኒቲ ካፍቴሪያ ውስጥ በተለያየ የሙያ ዘርፍ ሰማርተው እያገለገሉ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን አብዛኛዎቹ በወጣትነት እድሚያቸው የተቀጠሩ ናቸው። ታዲያ ለወጣትነት እድሜ ጉልበታቸው ሳይሰቱ ነገን በተስፋ በመናፈቅ ተመጣጣኝ ባልሆነ ክፍያ በቀን ከ 8 ሰዓት በላይ አውዳአመታትን ሳይቀር ያለ እረፍት በስራ በማሳለፍ [...]
↧