መግቢያ ከረዢም ዓመታት ጀምሮ ሃገራችንን የተናወጧት ሁለት እንደ ነቀርሳ በሸታ የሚሰረስሯትና ህልውናዋን ያዳከሟት ነገሮች በግልጽ ይታያሉ። አንደኛው ራሱ ታጋይ ነኝ የሚለው ምሁር መፍትሄ ፈላጊ መሆኑ ቀርቶ ችግር ፈጣሪ መሆኑ፤ ሁለተኛው ደግሞ ምሁሩ በሚፈልገውና በሚከተለው የትግል ስልት ዘንድ ያለመጣጣም መኖሩ። በፕሪንስፕል ደረጃ መከተል ባለብን መሰረተ-ሃሳቦች ዘንድና እንደ ዐላማ ለመድረስ በምንፈልጋቸው ነገሮች ለመጣጣም የማይችሉ ሁኔታዎች ተፈጥረው በብዙ [...]
↧