እርሳስ በጓደኛው፤ በብዕር እስክሪፕቶ ባለው ገደብ የለሽ፤ ነጻነቱ ቀንቶ እንዳሻው ቢናገር፤ የልቡን አውጥቶ እንዲህ አልክ ብሎ፤ ያለውን አጥፍቶ የሚያስወግድበት፤ በላጲስ አንሥቶ ስለማይከላ፤ ሲናገር አፍ ከፍቶ ፡፡ እሱ ግን ዘለዓለም፤ በላጲሱ ጠፍቶ መኖሩ አስመርሮት፤ በእጅጉ ተከፍቶ እኔስ ለምን እንዴት? ማለት ጀመረና ጠየቀ አፋጠጠ፤ ተሰማው ፍነና ነጻነቱን ሊያውጅ፤ ተነሣ ይሄ ጀግና ከእንግዲህ በኋላ፤ አለ ቆፍጠን ብሎ የነበረውን [...]
↧