ከጥቂት ሳምንታት በፊት ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን በተመለከተ በሥራ ጉዳይ እንግሊዝ አገር ተገኝተው የነበሩት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ሎንዶን የሚገኘው Minority Rights Group International ጽ/ቤት ባደረገላቸው ግብዣ ቃለምልልስ አድርገው ነበር፡፡ በቃለምልልሱ ወቅት ሁለተኛው የአፍሪካ የመሬት ነጠቃ እየተካሄደ እንደሆነ እና እንዲህ ዓይነቱ አስከፊ ተግባር እየተፈጸመ ያለው በእንግሊዝና ሌሎች ምዕራባውያን አገራት ዕርዳታና ድጋፍ [...]
↧