በምኒልክ ዘመን በኦሮሞ ተወላጆች ላይ ተፈፅሟል የተባለውን የጡትና እጅ መቁረጥ ኢ-ሰብአዊ ድርጊትና ጭፍጨፋ ለማስታወስ በሚል በአርሲ አኖሌ አካባቢ በ20 ሚሊዮን ብር የተሰራው ሃውልት፣ በቅርቡ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሙክታር ከድርን ጨምሮ በርካታ የኦህዴድ ባለስልጣናት በተገኙበት ተመርቋል፡፡ ሃውልቱን ያሰራው አካል ያለፈን ታሪክ መዞ ቂም በቀልን ለማውረስ ሳይሆን ቀጣዩ ትውልድ ከአስከፊው ድርጊት እንዲማርና ወደፊት ድርጊቱ እንዳይደገም ነው [...]
↧