ወቅቱ ረመዳን ነው፡፡ እነሆ ለረመዳን የሚሆን (አንድ ወግ) ልጋብዛችሁ፡፡ ኸሊፋው ዑመር ኢብን አል-ኸጣብ ዘወትር እንደሚያደርገው የነዋሪዎቹን ሁኔታ ለመታዘብ በምሽት በመዲና ጎዳዎች ላይ ይንጎራደድ ነበር፡፡ ወደ አንድ ሰፈር ሲደርስ በስካር መንፈስ የሚለፈልፍ ሰው ድምጽ ሰማ፡፡ ወደ ቤቱ ተጠግቶ በመስኮት ቢያይ ሰውዬው የወይን ጠጅ እየጠጣ ዓለሙን ሲቀጭ አገኘው፡፡ ዑመር አላስቻለውም፡፡ በመስኮት ዘሎ ገባና ሰውዬውን “አንተ ምን መስራትህ [...]
↧