የፕራይቬታይዜይሽንና የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ውሳኔ መስጠት በተቸገረበት የብሔራዊ ትምባሆ ድርጅት ሽያጭ ጉዳይ ላይ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ውሳኔ ሰጠ፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የየመኑ ኩባንያ ሼባ ኢንቨስትመንት የብሔራዊ ትምባሆ ድርጅት 60 በመቶ ባለቤት እንዲሆን ወስኗል፡፡ የ70 ዓመት ዕድሜ ባለቤት የሆነው ብሔራዊ ትምባሆ ድርጅት 22 በመቶ የሚሆነው አክሲዮን ከ1991 ዓ.ም. ጀምሮ [...]
↧