ፈላጊና ተፈላጊን የሚያገናኙ ደላሎች እስከ 60 ሺህ ብር ኮሚሽን ይከፈላቸዋል ባሎቻቸው ሳያውቁ በውጭ አገር ማህፀን አከራይተው የተመለሱ ሴቶች አሉ ማህፀን ማከራየትም ሆነ መደለል ህገወጥ ነው – የህግ ባለሙያ ማህፀን ለመከራየት ከአሜሪካና ከአውሮፓ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ባለትዳሮች በመበራከታቸው ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ እንደተስፋፋ ደላሎች የተናገሩ ሲሆን፤ የማህፀን ኪራይና የማህፀን ኪራይ ድለላ ህገ-ወጥ እንደሆነ የህግ ባለሙያ ገለፁ፡፡ [...]
↧