ባለፈው ሰሞን ወያኔ ኢሕአዴግ ላለመው የጥፋት ተልእኮ ወሳኝ ክንውኑን መተግበሩ ይታወሳል፡፡ ወያኔ ለጥፋት ተልእኮው በእጅጉ የሚረዳውን ወሳኝ የጥፋት ሥራ የመሥራቱን ያህል ከእምነተ-አሥትዳደር (ፖለቲካ) ፓርቲዎች (ቡድኖች) አንሥቶ እስከ ሕዝባዊ ማኅበራት (Civic organizations) ድረስ ያሉ ሁሉ ልብ ሳይሉት ወይም በቅጡ ሳይረዱት ቀርተው ይሁን ምን አላውቅም ተገቢውን ትኩረት ሳይሰጡት ሲቀሩ ሳይ እጅግ ተገርሜያለሁ፡፡ ወያኔ በአሩሲ ሔጦሳና በሐረር ጨለንቆ [...]
↧