ለአንድ ዘጠኝ ቀናት በግል ጉዳይ ምክንያት ወደ ገጠር ወጣ ብየ ነበር፡፡ ሀገር ሰላም ብየ ከሄድኩበት ስመለስ ከሁለት ወራት በፊት “የተገነቡትና በመገንባት ላይ ያሉ የመታሰቢያ ሐውልቶች የሠማዕታት ወይስ የቅሱፋን” በሚል ርእስ በጻፍኩት ጽሑፍ ምክንያት የዕንቁ መጽሔት ዋና አዘጋጅ ኤልያስ ገብሩ እና ዋና ሥራ አስኪያጁ ፈቃዱ ምኅተመወርቅ ማዕከላዊ ተብሎ በሚጠራው ፖሊስ ጣቢያ ተጠርተው ከሔዱ በኋላ መከሰሳቸው ተነግሯቸው [...]
↧