ሚስት ከቤቷ ጥጋ ጥግ ትንንሽ ጊዜያዊ ጉልቻ ጎልታ ካንዱ ወዳንዱ እየተዛወረች ስራዋን ስትሰራ፣ ስትቀቅል፣ ስታነኩር፣ ስትጋግር፣ ስትወጠውጥ … ድንገት ባንዱ አቅጣጫ እሳቱ መልኩን ቀየረ። ቀስ ብሎ ለካስ ወደ ቤቱ ተዛምቶ ነበርና ቤቱ ነደደ። እሳቱን ያዩ ለማጥፋት እየተሯሯጡ ደረሱ። አልሆነም የቤተሰቡ መኖሪያ ነደደ። ቤቱ የቆመው ለመቀጣጠል በሚያመች ማዋቀሪያ ነበርና ወደ አመድ ተቀየረ። ልክ እንደ ጎሳ ፖለቲካ!! [...]
↧