የአንድን ድርጅት ማንነቱን ከማቅረብ በፊት ቀደም ብሎ የተፈጸመውን ስህተት፣ ቀጥሎም ኢህአፓን ለማጥፋት በህወሓት እና በሻእቢያ የደረሰበትን ጥቃት አጠር ባለ መልኩ ማቅረብ አስፈላጊ ይሆናል። የስትራተጂ ስህተት ለከባድ ወድቀት ይዳርጋል ኢህአፓ ትግሉን የጀመረው ገና በ1960 መጀመሪያ ነበር። አብዮቱ እየተቀጣጠለ ሃገር አቀፍ ሆነ። ዘውዳዊ ስርዓት ወድቆ በማርክሲዝም ሌኒኒዝም ርእዮተ ዓለም የሚመራ ሶሻሊዝም የኢትዮጵያ ስርአት እንዲሆን ነበር። ይህ ግራ [...]
↧