መላ ሰውነቱ ይንቀጠቀጣል፤ ከንፈሩ ደርቋል። ለሁለት ቀናት ምግብ አላገኘም። ድንጋጤ አለቀቀውም። ከማይካድራ ግድያ አምልጦ ሁመራ ከተማ መከላከያ ሠራዊት ካምፕ በር ላይ ያገኘነው ወጣት ዳንኤል ማሚን። የደቡብ ክልል የቴፒ ተወላጅ ነው፤ አገር ሰላም ብሎ በማይካድራ ልብስ እየነገደ መኖር ከጀመረ 13 ዓመት ሆኖታል። በዚች ከተማ ይህን ያህል ሲኖር የከፋ አይደለም፤ ቀለል ያለ ችግርም አጋጥሞት አያውቅም። በሚኖርባትና ህይወቱን […]
↧