በድሬደዋ የፀጥታ አካላት በጋራ ባካሄዱት የክትትልና ቁጥጥር ስራ በህገ -ወጥ መንገድ የሚንቀሳቀሱ የሀገርን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት የገንዘብ ኖቶች መያዛቸው ተገለፀ። ገንዘቡ በቁጥጥር ስር የዋለው ትላንት መስከረም 6/2013 ዓ/ም ሲሆን ከህበረተሰቡ በተሰጠ ጥቆማ መሰረት ባደረገ ክትልል መሆኑን ድሬ ፖሊስ አስታውቋል። ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ 4 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በህግ መታየት መጀመሩም ተገልፃል። […]
↧