በድሉ ዋቅጅራ (ዶ/ር) “እንደቀልድ፣ ሳናውቀው አገራችን ወደ ፍርስራሽነት ተቀየረች” አለ፣ አንድ ታዋቂ የየመን ጋዜጠኛ፤ በአንድ ቃለመጠይቁ ላይ። ነገሮች የረዥም፣ ተከታታይ ሂደት ውጤት ወይም መጨረሻ ናቸው፤ የድንገቴ ክስተት አይደሉም። ጦርነት ያለመግባባትና የቅራኔ ሂደት ውጤት ነው። ሞት ከጤንነት ጀምሮ፣ እየጠነከረ የሚሄድ ህመም ሒደት ውጤት ነው። በሥርዓትና ደንብ የቆመ ሀገር መፍረስም እንዲሁ የረዥም ጊዜ፣ ተከታታይ ከሥርዓትና ደንብ ማፈንገጥ […]
↧