ከባርነት ሞትን የመረጥከው ወንዱ፣ አፉን ክፍት አርጎ የዋጠህ መቃብሩ፣ የማዋይህ አለኝ ስማኝ ሰማእቱ፡፡ የፈሰሰው ደምህ በህልሜ እየታየኝ፣ አጥንትህ ከመቃብር እየጎራበጠኝ፣ እሾህ ቀጋ ሆኖ አላስተኛህ አለኝ፡፡ ለፍትህ ስትጮህ የቀረኸው ባጭር፣ ጎንደር ደብረታቦር ወልድያ ባህርዳር፣ ቡሬና ዳንግላ ማጀቴና አቸፈር፣ ዛሬም ወንድሞችህ ታስረዋል ግዮን ዳር፡፡ በስናይፐር የፈጁህ ህሊና ቢሶቹ፣ ለውጥ አመጣን ብለው ያንኑ ደገሙ፣ አንድ አስገዳይ ነቅለው ሌላውን […]
↧