ጠንቋይና ፖለቲከኛ የሚያመሳስላቸው አንድ ነገር አለ። ሁለቱም ተገልጋያቸውን ለማምታታት የትኩረት አቅጣጫ ማስቀየርን ተክነውበታል። ኢሳያስ አፈወርቂ በዚህኛው – የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ – ገለጻቸው ራሳቸውን ሳይቀይሩ ሌላውን ለመቀየር የተነሱ ግብዝ ነው የሆኑት። ይህ “ቃለ-ምልልስም” አንድ አላማ አለው። አላማውን ለማወቅ ቃላቶችን መሰንጠቅም አያስፈልግም። ግልጽ ነው። ‘ብዙ ስላልተሰራበት’ መልዕክቱ የተጠበቀውን አላማ የመታ አይመስልም። ቃለ-ምልልሱ የተደረገበት ወቅት፣ የተመረጠበት ሰዓት የሚሰጠን […]
↧