ሚስጢሩ ወደኛ እየቀረበ ይሆን? የሚስጢሩን መጽሃፍ እያሳጠርኩ በመጻፍ ላይ እያለሁ ሚስጢሩን የሚአጠናክር ነገር ገጠመኝ። ከጓደኛዬ ጋር አልፈን አልፈን ውሃ የምንጎነጭባት ቤት አለች። እንደወትሮው በዛው ቤት ተገኝተናል። አንዲት ወጣት ስዊድናዊት ልታስተናግደን መጣች። ለጓደኛዬ የሞቀ ሰላምታ ሰጠችው። ስትስቅ ጉንጭና ጉንጮቿ ላይ የሚወጡት ጎድጓዳ ምልክቶች አይን ይስባሉ። ‹‹ባለፈው ጊዜ ስራ ለመቀጠር አስበሽ ያነጋገርኩሽ አይደለሽ?» አላት «አዎን! ተቀጠርኩ በጣም [...]
↧