ነሀሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ሰማያዊ ፓርቲ ታላቅ የተቃውሞ ሠልፍ መጥራቱ የሚታወቅ ነው፤ ይሁን እንጂ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት እንደሰፈር ጉልበታኛ ዱንኳን ሰባሪ ዘው ብሎ በሃይማኖት ስበብ ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው ቀንና ሰዓት እንዲሁም ቦታ በህግ አግባብ ሣይሆን በጉልበት ሠልፍ መሰል ሠልፍ ማካሄዱ የሚታወቅ ነው፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም [...]
↧