ባለፉት ፳፭(ሃያ አምሥት) ዓመታት በዐማራው ላይ የሚፈጸመው የዘር ማጥፋት እና የዘር ማጽዳት ዘመቻ ከችግሩ ሥፋት እናጥልቀት አንፃር ተመጣጣኝ የሆነ የሚዲያ ሽፋን አልተሰጠውም። በ«ኢትዮጵያዊነት» ስም በተቋቋሙት ድርጅቶችም ሆነ በተለያዩ አገሮች መንግሥታት ሥር የሬድዮ እና የቴሌቪዥን መርኃ-ግብሮችን በአማርኛ ቋንቋ የሚያሠራጩ ሚዲያዎች በዐማራው ላይ የሚፈጸመውን ግፍ እና በደል የዓለም ማኅበረሰብ እንዲያውቀው የማድረግ ፈቃደኝነታቸው እጅግ ውስን መሆኑን በተደጋጋሚ ታይቷል። […]
↧