ህውሃት (መንግስት) ህዝብን የሚገዛበት የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ አቅሙ ከሰማይ የሚወርድለት ወይንም በተፈጥሮው ከውስጡ የሚንጠፈጠፍለት ሳይሆን ከህዝብ የሚነጭለት ነው። ፖሊሱም፣ ደህንነቱም፣ የኢቲቪ ሰራተኛውም፣ የቃሊቲ አስተዳዳሪውም፣ የኢምባሲ ሰራተኛውም፣ ወ.ዘ.ተ. ከህዝብ የሚመለመሉ ናቸው። ለህውሃት በደሞዝ ክፍያ ያገልግሉ እንጂ የሰዎቹም ሆኑ የደሞዛቸው ምንጭ ህዝብ ነው። በግብር እና በሌሎች ምክንያቶች ከህዝብ የሚሰበሰብ ነው ደሞዛቸው። አሊያም በኢትዮጵያ ህዝብ ስም ከውጭ [...]
↧