በየአመቱ የካቲት 12 ቀን ሲደርስ ከማስታውሳቸው የዚህች አገር ባለውለተኞች መካከል ተመስገን ገብሬ አንዱ ነው። ይህ ሰው ሀገሩ ኢትዮጵያ በፋሽስቶች እንዳትወረር ብዙ ትግል አካሂዷል። ከወረራው በኋላም በአርበኝነት ተሰማርቶ የፋሽስቶችን ግብአተ-መሬት ካፋጠኑ የኢትዮጵያ ታላላቅ ደራሲያን መካከል ከግንባር ቀደሞቹ አንዱ ነው። ተመስገን ገብሬ በ1901 ዓ.ም ጐጃም ደብረማርቆስ ከተማ ነው የተወለደ። ታህሳስ 15 ቀን 1941 ዓ.ም በ40 ዓመቱ አረፈ። […]
↧