በኢትዮጵያ ውስጥ የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ ጉዳይ፣ የመሬት ላራሹ ጉዳይ ሙሉ መልስ ጠፍቶት እነሆ ግምሽ ምዕተ ዓመትን ፈጀብን። ዛሬም ግን ይህ ጥያቄ እንደገና ተቀጣጥሎ እልባት ካላገኘ አገራችን ከችግር ትወጣለች ማለት የማይሆን ነገር ነው። የመሬት ይዞታን ጉዳይ በተመለከተ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ወገኖች የተለያየ ኣሳብ ያላቸው ይመስላል። አንዱ ወገን ችግሩ መሬት የመንግስት መሆኑ ሳይሆን የመንግስት የፖለቲካ ቁርጠኝነቱ ዝቅተኛ […]
↧