እርቅን፣ ሰላምን፣ ፍቅርን፣ መቻቻልን ለማውረድ የሃይማኖት አባቶችና ሽማግሌዎች ቁልፍ ሚና አላቸው። በር ዘግተው ይጸልያሉ። ያስታርቃሉ። ይገስጻሉ። ያስጠነቅቃሉ። እንዲህ አይነት ለሌሎች ብርሃን ለመሆን የሚቃጠሉ የሃይማኖት አባቶች ያሏቸው ምንኛ የታደሉ ናቸው? በተቃራኒው የአምላክ ባሪያዎች፣ የየእምነታቸው ባሪያዎች፣ የምዕመናን መንፈስ መጋቢዎችና ጠባቂዎች፣ ወዘተ አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚወጡ በይፋ ተነገረን። “በተገንጣይ ነጻ አውጪ” ስም እየተጠራጠረና እየተጸየፈ አገራችንን ከሚመራ ከሃዲ ድርጅት [...]
↧