ዘመን ፊትሽ ተከምሮ እየታዬ ስራሽ አምሮ እንቁጣጣሽ አንድ ብለሽ አርባ ድረስ እድሜ ቆጥረሽ እንደ ቤቶች የሳቅ ተውኔት እንደ ጨቤ ስካር ህይወት ሞት ራሱን ያሾፍሽበት ለምንድነው? በይ ንገሪኝ እባክሽን አደብቂኝ ባንቺው ቀዬ የተወለድኩ ፊደል በጄ እዛው የያዝኩ መስፍን ሜዳ የተራገጥኩ በጨበጣ ብይ ያስቆጠርኩ ቲቸር ታዬ ያስተማሩኝ ገብሬ ኩርኩም ያቀመሰኝ የሲሚንቶ ጭስ ያወዛኝ ቅዱስ ያሬድ ተሳልሜ ከሽፋ […]
↧